የእምነት መግለጫ

ስለ እግዚአብሄር

ሰማይነና ምድርን እንዲሁም ጽንፈ አለሙን የፈጠረው እና የሚገዛ አምላክ ነው። እርሱ ክዘለአለም ጀምሮ የነበረ እና ራሱን በሶስትነት የገለጸም እርሱም አብ ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ ሲሆን እርሱም ሶስቱም እኩል እና አንድ አምላክ ናቸው። ዘፍ 1:1,26,27. 3:22, መዝ 90:2.; ማቲ 28: 19; 1ጴጥ. 1:2, 2. ቆሮ 13:14

ስለ መጽሃፍ ቅዱስ

መጸሃፍ ቅዱስ ለሰው ልጆች ሁሉ የተሰጠ የእግዚአብሄር ቃል ነው። ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ስር ሆነው የጻፉት ነው። ለክርስትና  እምነት የፍጹም እውነት ምንጭ እና ክርስቲያናዊ ሂወት መመሪያ ነው። በእግዪአብሄር መንፈስ ተነድተው ይጻፉት ስለሆነ ፍጹም እውነት የሆነ፣ የሚታመን እና ከስህትት የሌለበት ነው። 2.ጢሞ 3:16; 2ጲጥ 1:20 -21; 2ጢሞ. 1:13; መዝ. 119;105, 160; መዝ. 12:6; ምሳ.30:5

ስለ ሰው

ሰው የእግዚአብሄር የእጁ ስራ ሆኖ በርሱ መልክ የተፈጠረ ስለሆነ በፍጥረቱ እግዚአብሄረን ይመስላል። ሰው ከፍጥረታት ሁሉ የላቀ ተፈጥሮ አለው። ምንም እንኳ ሰው ትልቅ ችሎታ ቢኖረውም አንዱ መለያው ያልመታዘዝ ባህሪው ነው፣ ይህም ሃጢያት ይባላል። ይህ ሃጢያታዊ ባህሪ ደግሞ ከእግዚአብሄር ይለያል። ዘፍ.1:27; መዝ 8:3-6; ኢሳ 59:1,2; ኢሳ 53:6; ሮሜ 3:23

ስለ ዘለአለም

ሰው ለዘለአለም ይኖር ዘንድ ተፈጥሯል። ክአምላኩ ከእግዚአብሄር ጋር እንደተለየ ለዘለአለም ይኖራል ወይም በደህንነት እና የሃጢያት ስርየት ወይም ይቅርታ ክእግዚአብሄር ጋር ለዘለአለም ይኖራል። ከእግዚአብሄር ተለይቶ መኖር የዝለአለም ሞት ሲሆን፣ ከእግዚአብሄር ጋር መኖር ደግሞ የዝለአለም ሂወት ነው። ዮሃ.3:16; 2:25 ; 5:11 – 13; ሮሜ 6:23; ራዕ. 20;15; 1. ዮሃ 5:11 -12; ማቴ 25:31 -46

ስለ እየሱስ ክርስቶስ

እየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሄር ልጅ ነው። ከአብ ጋር እኩል አምላክ ነው። በመንፈስቅዱስ የተጸነሰ፣በስጋ የተገለጠ፣ ከድንግል ማርያም የተወለደ ነው። ራሱን ስለ አለሙ ሁሉ ሃጢያት ራሱን ንጹህ መስዋእት ያቀረበ፣ ይሞተ እናመ በሶስተኛው ቀን ክሙታን የተነሳ። ሞትን እና ሃጢያትን የረታ፣ ወደ ሰማይ ያረገ ደግሞ ዳግመኛ የነገስታት ንጉስ እና የጌቶቸ ጌታ ሆኖ የሚመለስ ነው። ማቲ. 1:22-23; ኢሳ 9:6, ዮሃ. 1:1-5; 14:10-30; ዕብ.4:14-15; 1. ቆሮ 15:3-4; ሮሜ 1:3-4; ሃዋ 1:9-11;1ጢሞ. 6:14 -15; ቲቶ 2:13

ሰለ ደህንነት

ደህንነት ለሰዎች ሁሉ ያቀረበው የእግዚአብሄር ነጻ ስጦታ ነው። ሰው በራሱ መንገድ መልካም ስራ እንዲሁም ሌላ መንገድ ሊድን አይችልም። ነገር ግን ሰው በክርስቶስ እየሱስ በሆነው እምነት በኩል በጸጋ ይድናል። የዘላለም ሂወት ሰው እየሱስ ክርስቶስን የሂወቱ ጌታ እና አዳኝ አድርጎ በእምነት ሲቀበል የዘላለምን ሂወት በዚያው ቅስበት ይጀምራል። ሮሜ 6:23; ኤፌ. 2:8 -9; ዮሃ. 14:6; ዮሃ. 1:12; ቲቶ3:5; ገላ.3:26; ሮሜ 5:1.

ስለ መንፈስ ቅዱስ

መንፈስ ቅዱስ ከአብ እና ከወልድ ጋር እኩል ነው። ስለ ከርስቶስ እየሱስ ክርስቶስ እንድንረዳ እንዲሁም እንደሚያስፈልገን ሊያስረዳን ባለንበት በዚህ አለም አለ። ሰው ደህንነትን ሲያገኝ መንፈስቅዱስ በአማኙ ውስጥ መኖር ይጀምራል። የአማኙን ሂወት በሃይል ይሞላል፣ መንፈሳዊ እውንትን እንዲረዳ እና ጽድቅ የሆነውን ነገር፣ ተክክለኛውን ነገር እንዲሰራ ይመራዋል። አማኙመ የእለት ተእለት ሂወቱን ለእርሱ በማስገዛት በምሪቱ ይኖራል። 2. ቆሮ 3:17; ዮሃ. 16:7-13; ዮሃ. 14: 16-17; ሃዋ 1:8; 1. ቆሮ. 3:16; ፌኤ.1:13; ገላ. 5:1.